ፕሮቲን ሰውነታችን በተገቢው መንገድ ተግባሩን እንዲያከናውን ከሚያግዙ ንጥረ ነገሮች መካከል ዋነኛው ነው።
ፕሮቲን በሰውነታችን ውስጥ የሚገኙ እያንዳንዱ ህዋሳት አካል ነው።
ሰውነታችን ፕሮቲን በመጠቀም ህዋሳትን ይገነባል፤ ያድሳል።
ኢንዛይሞችን፣ ሆርሞኖችንና ሌሎች የሰውነት ኬሚካሎችን ለመስራት፤ አጥንት፣ ጡንቻ እና ቆዳን ለመገንባትም ይውላል።
ሰውነታችን ካርቦሀይድሬት እና ስብ እንደሚያከማቸው ሁሉ ፕሮቲን አያከማችም።
በመሆኑም ሰውነታችን ጠቃሚ ንጥረ ነገር እንዲያገኝ በፕሮቲን የበለፀጉ ምግቦችን በየጊዜው መውሰድ ይኖርብናል።
ስጋ፣ ወተት፣ አሳ፣ እንቁላል፣ ጥራጥሬ፣ ቅቤ፣ ለውዝ እና የመሳሰሉት ዋነኛ የፕሮቲን ምንጮች ናቸው።
የጤና ባለሙያዎች በቀን ውስጥ ከምንወስደው ካሎሪ ከ10 እስከ 30 በመቶው የፕሮቲን ይዘት እንዲኖረው ይመክራሉ።
ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ነጥቦችም ሰውነታችን የፕሮቲን እጥረት እንዳጋጠመው ያመለክታሉ ተብሏል።
1. የአጥንት ጥንካሬ ማነስ
2. የፀጉር መርገፍ
3. የምግብ ፍላጎት መቀነስ
4. የእጅ እና እግር እብጠት
5. በሽታ የመከላከል አቅም መዳከም
6. የጥፍር ጥንካሬ ማነስ እና መሰነጣጠቅ
7. ቀልብን የመሰብሰብ ችግር
8. የእንቅልፍ እጦት
9. መደበኛ ያልሆነ የወር አበባ ኡደት
10. ለድብርት መጋለጥ
ምንጭ፦ www.minq.com/food
ፕሮቲን ሰውነታችን በተገቢው መንገድ ተግባሩን እንዲያከናውን ከሚያግዙ ንጥረ ነገሮች መካከል ዋነኛው ነው። ፕሮቲን በሰውነታችን ውስጥ የሚገኙ እያንዳንዱ ህዋሳት አካል ነው። ሰውነታችን ፕሮቲን በመጠቀም ህዋሳትን ይገነባል፤ ያድሳል። ኢንዛይሞችን፣ ሆርሞኖችንና ሌሎች የሰውነት ኬሚካሎችን ለመስራት፤ አጥንት፣ ጡንቻ እና ቆዳን ለመገንባትም ይውላል። ሰውነታችን ካርቦሀይድሬት እና ስብ እንደሚያከማቸው ሁሉ ፕሮቲን አያከማችም። በመሆኑም ሰውነታችን ጠቃሚ ንጥረ ነገር እንዲያገኝ በፕሮቲን የበለፀጉ ምግቦችን በየጊዜው መውሰድ ይኖርብናል። ስጋ፣ ወተት፣ አሳ፣ እንቁላል፣ ጥራጥሬ፣ ቅቤ፣ ለውዝ እና የመሳሰሉት ዋነኛ የፕሮቲን ምንጮች ናቸው። የጤና ባለሙያዎች በቀን ውስጥ ከምንወስደው ካሎሪ ከ10 እስከ 30 በመቶው የፕሮቲን ይዘት እንዲኖረው ይመክራሉ። ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ነጥቦችም ሰውነታችን የፕሮቲን እጥረት እንዳጋጠመው ያመለክታሉ ተብሏል። 1. የአጥንት ጥንካሬ ማነስ 2. የፀጉር መርገፍ 3. የምግብ ፍላጎት መቀነስ 4. የእጅ እና እግር እብጠት 5. በሽታ የመከላከል አቅም መዳከም 6. የጥፍር ጥንካሬ ማነስ እና መሰነጣጠቅ 7. ቀልብን የመሰብሰብ ችግር 8. የእንቅልፍ እጦት 9. መደበኛ ያልሆነ የወር አበባ ኡደት 10. ለድብርት መጋለጥ ምንጭ፦ www.minq.com/food