የኢትዮጵያ የንግድ ሚንስትር ዴኤታ ከዱባይ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር መክረዋል፡በተለይም በስጋ፣ በቀንድ ሀብት ልማት እንዲሁም በጨርቃጨርቅ እና በመሳሰሉት ዘርፎች የዱባይ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቦላቸዋል፡፡ከኢትዮጵያ የልማት ፖሊሲ ጋር በሚጠጣሙ ተግባራት የዱባይ ባለሀብቶችን ለማሳትፍ ዝግጁ መሆናቸውን ደግሞ ከዱባይ ባለስልጣናት በኩል ተገልጿል ፡፡ዱባይና ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት ባደረጓቸው የንግድ ስምምነቶች ሁለቱም ወገኖች ተጠቃሚ እየሆኑ መምጣታቸውን በውይይቱ ወቅት ተናግርዋል፡፡፡