በአድዋ ድል መሠረትነት የተገኘውን የሰላም የልማትና የመልካም አስተዳደር ግንባታን ስኬታማ ለማድረግ ሁሉም ህብረተሰብ የነቃ ተሳትፎ ሊያደርግ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ከንቲባ ድሪባ ኩማ አሳሰቡ፡፡ጀግኖች አርበኞች የዛሬ 121 ዓመት በማን አለብኝነት በመነሳሳት ኢትዮጵያዊያን ሲወር በአልበገር ባይነት ወራሪውን ጦር በፍፁም ቆራጥነት በመታገል ከኢትዮጵያ ጠራርጎ ለማስወጣት ከፍተኛ መስዕዋትነት ከፍለዋል፡፡ድሉ በተገኘበት 121ኛው ዓመት በዓል በኢዲስ አበባ ምኒሊክ አደባባይ በተለያዩ ስነ ስርዓቶች ተከብሯል፡፡በበዓሉ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከንቲባ ድሪባ ኩማ የአድዋ ድል በዓል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው አፍሪካ አንፀባራቂ ድል ነው ብለዋል ፡፡ጀግኖች አርበኞች ባስገኙት ድል የአሁኑ ትውልድ በተለያዩ የልማት ስራዎች ርብርብ እያደረገ መሆኑን የገለፁት አቶድሪባ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባ ታላቅ ማሳያ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡እናም ህብረተሰቡ እያደረገ ያለውን ተሳትፎ እንዲጠናክርም ጥሪ አቅርበዋል፡፡የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጅግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዝዳንት በተወካያቸው በኩል በድሉ የተገኘውን ውጤት ትውልዱ በድህነት ላይ ሊተገብረው እንደሚገባም ነው የገለፁት፡፡የበዓሉ ተሳታዎች በበኩላቸው አገሪቱ የጀመረችውን የዕድገት ጉዞ ለማፋጠን ሁሉም በተሰማራበት በቁርጠኝነት ሊሰራእንደሚገባም አሳስበዋል፡፡በበዓሉ አከባበር ላይ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ተሳታፊ ነበሩ፡፡