ዱባይ በዓለም ፈጣኗን ቡጋቲ ቨይሮን የፖሊስ መኪና ባለቤት ሆነች፡፡

የፖሊስ መኪናዋ በሰዓት 253 ማይል ወይም 407 ኪሎሜትር ትሽከረከራለች፡፡

የዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ ለዱባይ ፖሊሶች የዓለም ፈጣን መኪና ባለቤት መሆናቸውን ማረጋገጫ ሰጥቷዋል፡፡

ከቨይሮን የመኪና እሽቅድምድም አሸናፊዋ የስፖርት ተሽከርካሪ ጋር ተመሳስላለች፡፡

በሰዓት 407 ኪሎሜትር የምትጓዘው ይህች ተሸከርካሪ 1 ሺህ የፈረስ ጉልበት ያለው ባለ 16 ሲሊንደር ሞተር ተገጥሞላታል፡፡

dubai1.jpg

ይህ መሆኑ ደግሞ በሁለት ሰከንድ ከግማሽ ጊዜ ውስጥ ከዜሮ ተነስታ 60 ማይል በሰዓት የምትጓዝበትን ፍጥነት ይሰጣታል፡፡

ከዚህ ቀደም የጣሊያን ፖሊስ ኃይሎች የፈጣን ተሽከርካሪ ባለቤት ክብረወሰንን ይሰዘው ነበር፤ ተሽከርካሪያቸው ላምበርጊኒ ጋላራዶ ኤል560-4 ስትሆን በሰዓት 230 ማይሎችን ወይም 370 ኪሎ ሜትሮችን ትምዘገዘግ ነበር፡፡

አሁን የተዋወቀቺው የዓለም ፈጣኗ የዱባይ ፖሊስ ተሸከርካሪ ወንጀለኛን በፍጥነት አጥምዶ ለመያዝ ሳይሆን በዱባይ የገበያ ስፍራ እና የባህር ዳርቻዎች የጎብኝዎችን ቀልብ ለመሳብ እና ደህንነታቸው የተረጋገጠ መሆኑን ለማሳየት ነው፡፡

dobai3.jpg

የተሸከርካሪዋ መተዋወቅ ዋና ዓላማ በህዝቡ እና በፖሊስ ኃይሎች መካከል ያለውን ክፍተት መሙላት ሲሆን፥ የዱባይ ፖሊሶች ከጎብኝዎች ጋር ያላቸውን ቅርርብ ለማጠናከር መሆኑን የዱባይ ፖሊስ የትራንስፖርት ክፍል ጀነራሉ ሜጀር ሱልጣን አል ማሪ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም ከስርዓተ ጾታ ጋር በተያያዘ ያለውን የግንዛቤ ክፍተት ለመቅረፍ የጾታ እኩልነት መኖሩን ለማስተዋወቅ ያለመ ነው ብለዋል፡፡

dubu.jpg

ለዚህም ማሳያ እንዲሆን በጣም ውድ የሆኑት ፌራሪ እና ቤንትሌይ ተሸከርካሪዎች በሴት ፖሊሶች እንደሚሽከረከሩ ነው የገለፁት ሱልጣን፡፡

የአሽከርካሪነት ሙያው ባለቤት ለመሆን ባልብዙ ልሳን እና ተግባቢ መሆን አንዱ መስፈርት ነው ያሉት ሱልጣን አሽከርካሪዎች ተዝናኖትን የመፍጠር ጥሩ ችሎታ ሊኖራቸው እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

ሱልጣን እንደሚሉት አንዳንድ ሰዎች እንደውም በቀልድ መልኩ ፖሊሶችን እባካችሁ እሰሩኝ እያሉ በፖሊስ መኪና ውስጥ ገብተው ይንቀሳቀሳሉ፡፡

የዱባይ ፖሊስ ተሸከርካሪዎች ላምበርጊኒ አቬንታዶር ከተዋወቀችበት ከ2013 ጀምሮ የከተማዋን ጎብኝዎች በመማረክ እና ስራቸውን በማስተዋወቅ ረገድ የተሳካላቸው ሆነዋል፡፡

በዚህ የዱባይ ፖሊስ ተግባር በርካታ መኪና አምራች ኩባንያዎች ምርቶቻቸውን ለማስተዋወቅ በማሰብ እንስራላችሁ የሚል ጥያቄን እንዳቀረቡላቸው ገልፀዋል ኃላፊው፡፡

ለአካባቢ ጥበቃ ውጤታማነት በፈረንጆች 2030 ለታቀደው 25 በመቶ የሚሆኑ ተሽከርካሪዎችን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ እንዲሆኑ የማድረግ እቅድ አንድ አካል በመሆኑ የዱባይ ፖሊስ መስሪያ ቤት የኤሌክትሪከ መኪናዎችን ነው የሚገዛው፡፡

ምንጭ፡-ሲ ኤን ኤን