በብሪታንያ 19 ልጆችን የወለዱት እናት 20ኛ ልጃቸውን ወልደው ለመሳም እየተጠባበቁ ነው።

የ42 ዓመቷ እናት ሱ ራድፎርድ እና የ46 ዓመቱ ኖኤል በመጪው መስከረም ወር 20ኛ ልጃቸውን ወልደው እንደሚስሙ ለፌስቡክ ተከታዮቻቸው ይፋ አድርገዋል።

የእነ ራድፎርድ ቤተሰብ 19ኛ ሴት ልጃቸው ቤተሰቡን የተቀላቀለችው ባለፈው ሀምሌ ወር ነበር።

የሪያሊቲ ቲቪ ሾው ኮከቦቹ ሱ እና ባለቤቷ ሃሌ አላፊያ ቤው የተባለችውን ሴት ልጃቸውን በፈረንጆች 2015 ሰኔ ወር ላይ ከወለዱ በኋላ ልጅ የመጨመር ፍላጎት እንደሌላቸው ገልፀው ነበር።

ሆኖም በመጪው መስከረም የምትወለደው ወይም የሚወለደው ህጻን 10 ወንድሞች እና 9 እህቶች ይኖረዋል ወይም ይኖራታል።

የዓለማችን ብዙ አባላት ያሉት ቤተሰብ በህንድ ባክትዋንግ ሲሆን አባወራ ዚኦና ቻና ከ39 ሚስቶች 94 ልጆች ወልደዋል።

እኚህ አባት 14 ምራቶች እና 33 የልጅ ልጆች አሏቸው።

ምንጭ፡-www.mirror.co.uk