የአውሮፕላን ጥገና ማዕከሎቹ B747-800 አውሮላንን ጨምሮ የቦይንግ ትላልቅ አውሮፕላኖችን እንዲሁም በአንድ ጊዜ ከአንድ በላይ አውሮፕላኖችን የማስተናገድ አቅም አለው፡፡
ከጥገና ማእከሎቹ አንደኛው B777-200 አልያም B737 የቦንግ አወሮፕላኖችን ማስተናገድ ይችላል፡፡
ማእከሎቹ በሰፊ ቦታ ላይ ያረፉ ሲሆን በጣም ከፍታ ያለው ጣርያና የአውሮፕላን አጠቃላይ ጥገና ለመስጠት የሚያስችል አወቃቀር ያላቸው ናቸው፡፡ ከበስተጀርባ 15,000ሜ² ላይ ያረፈ የቢሮና የተለያዩ ሱቆች ቦታ መዘጋጀቱም ተገልጿል፡፡፡፡
ሪፖርተር፤ ብርሃን እያየው