የፀሎተ ሀሙስ በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርሰቲያን እና በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የኢየሱስ ክርስቶስ ትህትና እየታሰበ በተለያዩ ስነ ስርኣቶች እየተከበረ ነው።
ክርስቶስ በዛሬዋ እለት የሃዋርያትን እግር ዝቅ ብሎ በማጠብ ትህትናን እና ታዛዥነት ማስተማሩን በማሰብ ነው በዓሉ የሚከበረው።
በአሁኑ ሰዓትም በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ስነስርዓቱ እየተከናወነ ነው።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የብፁዕ ጳጳሳቱን እግር፥ ጳጳሳቱ ቆሞሳቱ እና ካህናቱም የምዕመናኑን እግር በማጠብ የኢየሱስ ክረስቶስን አርአያነት ተከትለው ስርዓቱን የመፈጸሙ ሰነስርዓት እእየተካሄደ ይገኛል፡፡
በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያንም ብጽእ ካርዲናል ብርሃነየሱስ ሱራፌል ሊቀ ጳጳሳት ዘካቶሊካዊያን በተገኙበት፥ በልደታ ማሪያም ካቶሊክ ካቴድራል በዓሉ እየተከበረ ይገኛል ።
የህፅበተ እግር ስነ ስርዓቱም ከጥቂት ሰዓት በኋላ ይካሄዳል።