ከሊቢያ ባህር ዳርቻ በሜዲትራኒያ ባህር ላይ ትጓዝ ነበረች ጀልባ ሰምጣ በትንሹ 97 ሰዎች መጥፋታቸው ተነገረ፡፡
የሊቢያ የጠረፍ ጠባቂን ጠቀሶ አልጀዚራ እንደዘገበው፥ ከሊቢያ ትሪፖሊ በ10 ኪሎሜተሮች ርቀት ላይ ጀልባዋ ከሰመጠች በኋላ 23 ስደተኞች ማዳን እንደተቻለ ታውቋል፡፡
ጀልባዋ ተለያዩ አፍሪካ ሀገራት ሰደተኞችን አሳፍራ ወደ አውሮፓ እያመራች በለበት ወቅት በድንገት ባህር ውስጥ ሰምጣለች፡፡
ከአደጋው በኋላ ሳይሰምጡ እንዳለቀረ የተጠቀሱት 97 የሚሆኑ ስደተኞች የጠፉ ሲሆን ፥ ከነዚህም 15 የሚሆኑት ሴቶች እና 5 ህጻናት እንደሚገኙበት ተጠቅሷል፡፡
እስካሁን ያልተገኙት ሰዎች የመትረፍ እድላቸው የመነመነ መሆኑ እና ፍለጋውን ለማካሄድ የአየር ሁኔታው አስቸጋሪ እንዳደረገው የሊቢያ ጠረፍ ጥበቃ ቃል አቀባይ አዮብ ቃሲም ተናግረዋል፡፡
ሊቢያ ከሜዲትራኒያ ወደ አውሮፓ የሚሸጋገሩ የ ስደተኞች ተመራጭ ብትሆንም ፥ባብዛኛው ስደተኞቹ ህይወታቸውን አደጋ ላይ በሚጥል እንዲህ ባለ ጉዞ ህይወታቸውን ሲያጡ በተደጋጋሚ ይሰማል፡፡
በዋነኝነት ስደተኞቹ የሚመጡት ከሰሃራ በታች ከሚገኙ የአፍሪካ ሀገራት ሲሆን፥ በህገወጥ የሰዎች ዝውውር በተካኑ ቡድኖች በጀልባ ተሳፍረው ከሊቢያ በ300 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ወደ ምትገኘው የጣሊያኗ ደሴት ላምባዱሳ ይጓዛሉ፡፡
የአለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት መረጃ መሰረት ፥ በአውሮፓውያን አዲስ አመት መባቻ ጀምሮ 590 ሰዎች ሞተዋል አልያም ጠፍተዋል ፡፡
እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር 2016 በአንድ አመት ብቻ 5ሺህ ሰዎች በባሀር ሲጓዙ ህይወታቸውን አጥተዋል ፡፡
በዚህ አመት በሶስት ወር ብቻ ከ24 ሺህ በላይ የሚቆጠሩ ስደተኞች ከሊቢያ ወደ ጣሊያን ገብተዋል፡፡
ባለፈው የካቲት ወር የአውሮፓ ህብረት ሰደተኞች በሊቢያ በኩል አቋርጠው ወደ አውሮፓ እንዳይገቡ 215 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የህብረቱ መሪዎች እና ሊቢያ መፈራረማቸው ይታወሳል፡፡
ምንጭ ፦አልጀዚራ