አሜሪካ በአይነቱ ግዙፍ የሆነ ቦንብ በአፍጋኒስታን በሚገኝ የአይ ኤስ አይኤስ ይዞታ ላይ ጥላ 36 የቡድኑ አባላትን መግደሏን አስታወቀች፡፡
አሜሪካ በአፍጋኒስታን ናንጋርሃር በተሰኘው የአይ ኤስ ይዞታ ላይ ያፈነዳችው የቦንብ አይነት አሜሪካ “የቦምቦች እናት” ብላ የምትጠራውና በጦርነት አውድ ላይ ከኒውከለር ቦንብ በመቀጠል ከጠቀመቻቸው የቦንብ አይነቶች ኃይለኛው ነው ተብሏል፡፡ቦንቡ 9ሺ 8ዐዐ ኪሎ ግራም ይመዝናል፡፡
የአፍጋኒስታን የመከላከያ ሚንስቴርም በጥቃቱ 36 የአይ ኤስ አባላት መገደላቸውን አረጋግጧል ፡፡ በሰላማዊ ዜች ላይ ግን ምንም አይነት ጉዳት አለመድረሱንም ሚኒስቴሩ አመልክቷል፡፡
የቀድሞው የአፍጋኒስታን ፕሬዝዳንት ሃሚድ ካርዛይ የአሜሪካን ጥቃት “ሰብዓዊነት የጎደለውና በአገራችን ላይ ጭካኔ የተሞላት ድርጊት ፈፅማለች” ሲሉ አውግዘዋል፡፡
ይሁንጂ የአፍጋኒስታን መንግስትና አሜሪካ የአሸባሪ ቡድኑን የጦር መሳሪያ ዶግ አመድ ለማድረግና በሰላማዊ ዜጎች ላይ ምንም አይነት ጉዳት እንዳያደርስ በጥንቃቄ የተካሄደ ዘመቻ ነው ብለዋል፡፡
በጥቃቱም የቡድኑን መሪ ጨምሮ ዋና ዋና አባላቱ በዒላማው መገደላቸውን ገልፀዋል፡፡
ምንጭ ፤ ቢቢሲ