በጀርመን የመጀመሪያ የተባለ “ሀይድሬል“ የተሰኘ በሀይድሮጂን ኃይል የሚሰራ ባቡር ተሰርቶ የመጀመሪያ ሙከራ ተደረገ፡፡

ባቡሩ ድምጽ አልባ መሆኑን እና  አካባቢን የማይበክል መሆኑ ተነግሮለታል፡፡

አዲሱ ባቡር በዲዝል ዘይት ከሚሰራ ባቡር በ60 በመቶ ድምጹ የቀነሰ ነው ተብሏል፡፡

ባቡሩ በፍጹም ጭስ የሌለው ሲሆን ፥ብቸኛ የሚያወጣው ድምጽ የሚሰማው ከባቡሩ መዘውሮች እና የንፋስ ግፊት መሆኑን የባቡሩን ለሙከራ ያቀረበው ፈረንሳዊ አምራች አስታወቋል፡፡

“ሀይድሬል“ አሰራሩ ልክ የዲዝል ዘይት እንደሚጠቀመው ባቡር ቢሆንም ፥ለየት የሚያደርገው በዲዚል ፋንታ ሀይድሮጂንን በሃይልነት መጠቀሙ ነው፡፡

በባቡሩ አናት ላይ የሚቀመጠው የነዳጅ ማስቀመጫ ውስጥ ሀይድሮጂን እና ኦክሲጅን በማዋህድ የኤሌክትሪክ ሃይል ተለውጦ ወደ ባቡሩ ባትሪ ይገባል፡፡

በለሁለት ፍርጎው ባቡር 207 ፓወንድ ታንክ ሃይደሮጂን የሚፈልጉ ሲሆን፥ በአንድ ነጠላ ሙሌት 300 መንገደኞችን 500 ማይሎች ድረስ ያጓጉዛል፡፤

የመጀመሪያው ባቡር እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2018 ስራውን ይጀምራል፡፡

ይህም ቴክኖሎጂ በአሁኑ ወቅት በጀርመን በስራ ላይ ከሚገኙትን 4 ሺህ የዲዝል ባቡሮች አካባቢን የማይበክል በመሆኑ በቀጣይ አመታት ይተካቸዋል ተብሎ ይታሰባል፡;

እንደ አውሮፓ ህብረት መረጃ በአውሮፓ 20 በመቶ የሚሆኑት ባቡሮች በዲዝል ዘይት የሚሰሩ ናቸው፡፡

ምንጭ፦ሲኤንኤን