የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መራዘም – በህገ መንግስቱ ዓይን
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መራዘም ከፖለቲካና ከህግ አንጻር እንዴት ይታያል? የህግ ባለሙያዎች የአዋጁ መራዘም ከህገ መንግስት ውጪ ነው ሲሉ ይሞግታሉ፡፡ ፖለቲከኞች በበኩላቸው፤ህዝቡ ህገ መንግስታዊ መብቱን ተነፍጎ ወታደራዊ አገዛዝ በሚመስል ሁኔታ ውስጥ ወድቋል ይላሉ፡፡ የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ አለማየሁ አንበሴ፣ ፖለቲከኞችንና የህግ ባለሙያዎችን አነጋግሮ አስተያየታቸውን እንደሚከተለው አጠናቅሮታል፡፡ ‹‹አስቸኳይ ሁኔታ በሌለበት አስቸኳይ አዋጅ አይታወጅም›› አቶ ተማም አባቡልጉ (የህግ ባለሙያ) በአጠቃላይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሲባል መጀመሪያ አስቸኳይ ሁኔታ መኖር አለበት፡፡ ይሄ ሲኖር ነው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚታወጀው። አስቸኳይ ሁኔታ በሌለበት አስቸኳይ አዋጅ አይታወጅም፡፡ በኢትዮጵያ ወቅታዊ እውነታ አስቸኳይ ሁኔታ በሌለበት ቦታ ሁሉ አዋጁ መታወጁ፣ አስቸኳይ አዋጅ አስፈላጊ እንዳልነበረ ያሳያል፡፡ አዋጁ የፖለቲካ ፍላጎትን ማሳኪያ ነው የሆነው፡፡...
Read More