በሊቢያ ባህር ዳርቻ አቅራቢያ አንዲት ጀልባ ላይ በደረሰ አደጋ 97 ስደተኞች ጠፍተዋል
ከሊቢያ ባህር ዳርቻ በሜዲትራኒያ ባህር ላይ ትጓዝ ነበረች ጀልባ ሰምጣ በትንሹ 97 ሰዎች መጥፋታቸው ተነገረ፡፡ የሊቢያ የጠረፍ ጠባቂን ጠቀሶ አልጀዚራ እንደዘገበው፥ ከሊቢያ ትሪፖሊ በ10 ኪሎሜተሮች ርቀት ላይ ጀልባዋ ከሰመጠች በኋላ 23 ስደተኞች ማዳን እንደተቻለ ታውቋል፡፡ ጀልባዋ ተለያዩ አፍሪካ ሀገራት ሰደተኞችን አሳፍራ ወደ አውሮፓ እያመራች በለበት ወቅት በድንገት ባህር ውስጥ ሰምጣለች፡፡ ከአደጋው በኋላ ሳይሰምጡ እንዳለቀረ የተጠቀሱት 97 የሚሆኑ ስደተኞች የጠፉ ሲሆን ፥ ከነዚህም 15 የሚሆኑት ሴቶች እና 5 ህጻናት እንደሚገኙበት ተጠቅሷል፡፡ እስካሁን ያልተገኙት ሰዎች የመትረፍ እድላቸው የመነመነ መሆኑ እና ፍለጋውን ለማካሄድ የአየር ሁኔታው አስቸጋሪ እንዳደረገው የሊቢያ ጠረፍ ጥበቃ ቃል አቀባይ አዮብ ቃሲም ተናግረዋል፡፡ ሊቢያ ከሜዲትራኒያ ወደ አውሮፓ የሚሸጋገሩ የ ስደተኞች...
Read More