ፅንስ ማስወረድ ጥርስ የመንቀል ያህል ቀሏል
ትምህርቷን ከዘጠነኛ ክፍል አቋርጣ የትውልድ መንደሯን ጥላ በስደት አዲስ አበባ እንድትመጣ ያስገደዳት ሳይታሰብ ድንገት የተፈጠረ እርግዝና ነው፡፡ ተወልዳ ባደገችበት ደብረብርሃን ከተማ፣ አብሯት ካደገው የልጅነት ጓደኛዋ ጋር ፍቅር የጀመሩት ገና በለጋ ዕድሜያቸው ነበር፡፡ ግንኙነታቸው ከጓደኝነትና ከከንፈር ወዳጅነት አልፎ አንሶላ ለመጋፈፍ ሲያበቃቸው ዕድሜያቸው ገና በአስራዎቹ መጨረሻ አካባቢ ላይ ነበር፡፡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን መማር በጀመሩ ጥቂት ወራት ውስጥ በድብቅ የፈፀሙትን የፍቅር ግንኙነት ገሃድ የሚያወጣ ድንገተኛ ነገር ተከሰተ፡፡ የአስራ ስድስት ዓመቷ ሰናይት /ለዚህ ፅሁፍ ስሟ የተቀየረ/ በዕድሜ 3 ዓመት ከሚበልጣት የልጅነት ፍቅረኛዋ ማርገዟን አወቀች፡፡ ሁኔታው እጅግ አስደንጋጭ ነበር፡፡ ሰማይ ምድሩ ዞረባት። የትውልድ አካባቢዋ ከጋብቻ በፊት የሚከሰት እርግዝናን አጥብቆ የሚጠላና የሚጠየፍ መሆኑን ጠንቅቃ ስለምታውቅ፣...
Read More