“ዓለም ‘ፌይር’ አይደለችም”
ስሙኝማ…በደስተኝነት ከዓለም 119ኛ ሆንን! ይቺን ይቺንማ ዝም ብለን አናልፍም፡ ልክ ነዋ… ከፈለገ ‘ኤይድ’ ምናምን የሚሉት ነገራቸው ይቀራል እንጂ እንዲህማ ‘ለፍቶ መና’ አያደርጉንም! እናማ…እኛ በጣም ‘ደስተኞች’ መሆናችንን ዓለም እንዲያውቅልን መከራችንን እያየን፣ እዛ ታች አውርደው የሚፈጠፍጡን ለምንድነው! የፈረንጅ ምቁነት የሚያበቃው መቼ ነው! ቂ…ቂ…ቂ… ቆይማ…የሌሊቱ ሰዓት አልበቃ እያለን ቀኑን ሙሉ የቡና ቤቶችን ውስጥና በረንዳ ሳይቀር እያጨናነቅን የምንውለው ‘ቢከፋን’ ነው! እግራችንን ሰቅለን ‘ሲፕ’ ከማድረግ የባሰ ምን ደስተኝነት አለ! እነሱ እንደየ አገራቸው ስርአት ዳንስ ቤቱና ቡና ቤቱ ሌሊት በስድስትም፣ በስምንትም ሰዓት ይዘጋልና እዚህ ‘የ24 ሰዓት አገልግሎት’ እየተሰጠ… አለ አይደል… እንዴት ነው በደስተኝነት ጭራው አካባቢ ናችሁ የሚሉን! እኔ የምለው… ይኸው አዳዲሱን የቴሌቪዥን ጣቢያ ሁሉ ዘፈን፣...
Read More