«ዓለምን ለማዳን የሚያስችል ኃይል የሚገኘው ከፍቅር ነው» – አልበርት አንስታይን
ፍቅር በዓለም ላይ ካሉ ህልዮቶች ሁሉ የላቀው ነው። ሰውን ጨምሮ ማናቸውም ፍጥረታት ከፍቅር ጋር አንዳች ምስጢራዊ ውህደት ያላቸው ይመስላል። ይህም ህይወት ራሷ ያለ ፍቅር የማትታሰብ በመሆኗ ከፍቅር ጋር የመሰረተችው ወዳጅነት ነው። ከአፏ የደረሰን ምግብ ለልጇ የምታጎርስ ወፍን የተመለከተ ፍቅር ምን ያህል ለህይወት አስፈላጊ ኃይል መሆኑን ይታዘባል። የምድራችን ታላቁ ፍጥረት የሆነውን ሰውንም ስናስብ መላ ህይወቱ ከፍቅር ጋር የተሳሰረ መሆኑን እንረዳለን። ባልና ሚስትን፣ ወላጆችንና ልጆችን እህትና ወንድሞችን አስተሳስሮ የአገር መሠረት የሆነውን ቤተሰብን የፈጠረው ፍቅር ነው። እግሬን ለጠጠር ግንባሬን ለጦር ብሎ ሰው ክቡር ህይወቱን የሚሰዋው እትብቱ ለተቀበረባት፣ ከአለመኖር ወደ መኖር ሲመጣ እጇን ዘርግታ ለተቀበለችው ለተወለደባት ለተገኘባት ምድር፣ ለእናት አገሩ ባለው ፍቅር ነው።...
Read More