የብሪታኒያ ተመራማሪዎች በዓለም ፈጣኑን የቲቢ መመርመሪያ ዘዴ አገኙ
በብሪታኒያ የኦክስፎርድ እና የበርሚንግሃም ተመራማሪዎች የቲቢ በሽታን በአጭር ጊዜ የሚለይ የዲኤንኤ የምርመራ ውጤቶችን በፍጥነት ማግኘት የሚያስችል ዘዴ ይፋ አድርገዋል። ተመራማሪዎቹ ጄኖም ሲኩዌንሲንግ በተባለ የምርመራ ስልት የበሽታውን እያንዳንዱን ጎጂ ህዋስ ዲኤንኤ በአጭር ጊዜ መለየት ችለናል ነው ያሉት፡፡ግኝቱ የቲቢ ህሙማኑ በሽታው ታውቆ መድሃኒቱን ለመጀመር ይወስድባቸው የነበረውን ረጅም ጊዜ በጥቂት ቀናት እንዲጀምሩ የሚያስችል የምርምር ውጤት መሆኑ ነው የተጠቀሰው። ጄኖም ሲኩዌንሲንግ የምርመራ ሂደት የተለያዩ የዲኤንኤ ናሙናዎችን በመውሰድ ከሳምንት በማይበልጥ ጊዜ ውስጥ የምርመራ ውጤቱን እንዲያገኙ እና መድሃኒት እንዲጀምሩ የሚያስችል ነው፡፡ የቲቢን በሽታ በፍጥነት መርምሮ ውጤቱን ማግኘት ህሙማኑ ቶሎ መድሃኒት እንዲጀምሩ በማድረግ በሽታው እንዳይጠነክር እነሱም እንዲድኑ ለማድረግ ይረዳል፡፡ይህ ባይሆን ግን በምርመራ መራዘም ምክንያት በሽታው በህሙማኑ...
Read More