በአዲስ አበባ በቤንዚን አቅርቦት ችግር ለእንግልት መዳረጋቸውን አሽከርካሪዎች ገለፁ
በአዲስ አበባ በሚገኙ ነዳጅ ማዳያዎች በተፈጠረ የቤንዚን አቅርቦት ችግር ለእንግልት መዳረጋውን አሽከርካሪዎች ገለፁ፡፡ ባለፉት 3 እና 4 ቀናት በአዲስ አበባ የሚገኙ ነዳጅ ማደያዎች ረጃጅም የተሽከርካሪ ሰልፎች ሲያስተናግዱ ተስተውለዋል᎓᎓ ችግሩም በቤንዚን አቅርቦት ላይ እየተስተዋለ መሆኑን ነው ኢቢሲ ያነጋገራቸው አሽከርካሪዎች የገለፁት᎓᎓ የታክሲ አገልግሎት የሚሰጥ አንድ አሽከርካሪ የተፈጠረው ችግር በስራው ላይ እቅንቅፋት እንደሆበት ለኢቢሲ ተናግሯል፡፡ “ቢያንስ እኔ የቆምኩት ከ2 ሰአት በላይ ሁኖኛል፤ ከቤተመንግስት አካባቢ ነው የመጣሁት ፡፡የተጨመረው ተጨምሮ ቤንዚኑ በቶሎ ይድረስልን” ሲል ጠይቋል᎓᎓ የነዳጅ ማደያዎች ግን የአቅርቦት ችግር ያለመኖሩን ነው የሚገልፁት᎓᎓በማደያዎቹ አካባቢ ሰልፉ መኖሩን አምነው ምክንያቱ ምን እንደሆነ ግን እንደማያውቁ ተናግረዋል፡፡ የማዕድን ፣ነዳጅና ተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር ችግሩ የአቅርቦት ሳይሆን ኢታኖል የተቀላቀለበት ቤንዚን...
Read More