የዕድሜ ባለ ፀጋው ዴቪድ ሮክፌለር ሕልፈት
በሕይወት ዘመናቸው ሙሉ በአገር ውስጥና በውጭ አገሮች ግንኙነት ዙሪያ በተቀረፁ ፖሊሲዎች ውስጥ በመግባትና ቡድን በማዋቀር ሠርተዋል፡፡ ካርኒጊ ኢንዶውመንት ፎር ኢንተርናሽናል ፒስ ውስጥ ከ34ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዲዋይት አይዘንአወር፣ ከአይቢኤም ፕሬዚዳንት ቶማስ ዋትሰን፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን ለመመሥረት ከተሳተፉትና በኋላም ለቀድሞዋ ሶቪየት ኅብረት ሰልለዋል ከተባሉት የአሜሪካ ባለሥልጣን አልገር ሄስ፣ እንዲሁም ከ52ኛው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ፎስተር ዳላስ ጋር በመሆን በቦርድ አባልነት አገልግለዋል፡፡ በአሜሪካ ከታዋቂው የንግድ ሰው ሶል ሊኖውትዝና ከሌሎችም ጋር በመሆን በደሃ አገሮች ቀጣይነት ያለው ልማት ለማምጣትና የግሉን ዘርፍ ለማበረታታት፣ ለትርፍ የማይሠራውን ዓለም አቀፍ ኤግዙኪዩቲቭ ሰርቪስ ኮርፕ ካቋቋሙዋቸው ድርጅቶች ውስጥ ይጠቀሳሉ፡፡በአገራችን አንድ ሰው ገንዘብ ካለውና ሲበትን ከተስተዋለ ‹‹ሮክፌለር ነው!›› እንደሚባለው ዓይነት...
Read More