የጃፓን አዛውንቶች የመንጃ ፈቃዳቸውን ከመለሱ የቀብር ወጪያቸው ሊቀነስላቸው ነው
የጃፓን መንግስት በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ እየተጨመረ የመጣውን የትራፊክ አደጋ ለመቀነስ የእድሜ ባለጠጎች የመንጃ ፈቃዳቸውን እንዲመልሱና ማሽከርከር እንዲያቆሙ በመጠየቅ ላይ ነው። ለዚህም ይመስላል አዛውንቶች ማሽከርከር ካቆሙ ወይንም መንጃ ፈቃዳቸውን ከመለሱ የቀብር ማስፈፀሚያ ወጪያቸው ላይ ቅናሽ ይደረግላቸዋል የተባለው። በማዕከላዊ ጃፓን አይቺ ግዛት ነው አንድ 89 የመቃብር ቤቶችን የሚያስተዳድረው ኩባንያ የመንጃ ፈቃዳቸውን ለሚመልሱ አዛውንቶች የ15 በመቶ ቅናሽ ማድረጉን ያስታወቀው። ኬይዶ የተባለ የዜና አገልግሎት እንደዘገበው፥ ማንኛውም መንጃ ፈቃዱን መመለስ የሚፈልግ የእድሜ ባለጠጋ በአካባቢው ወደሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ በመሄድ በማመልከት የቅናሹ ተጠቃሚ መሆን ይችላል ተብሏል። ቅናሹ የማዕከላዊ አይቺ ግዛት ነዋሪ ያልሆኑ ነገር ግን ቤተሰቦቻቸው በዚያው የሚገኙ ሰዎችንም ተጠቃሚ ያደርጋል ነው የተባለው። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2015...
Read More