ጉንፋንን በቤት ውስጥ ማከሚያ መንገዶች
ጉንፋን በአብዛኛው በቫይረስ አማካኝነት የሚተላለፍ በሽታ ነው።ጉንፋን የተለመደ በሽታ እንደመሆኑ መጠን ምናልባትም በአመት ሁለት እና ከዚያ በላይ ለሆነ ጊዜ ለዚህ በሽታ የመጋለጥ እድል መኖሩን ጥናቶች ያመለክታሉ። ጉንፋንን ሙሉ በሙሉ ማስቀረት ባይቻልም ማከም እና መከላከል ግን ይቻላል፤ ለዚህ ደግሞ አብዛኛውን ጊዜ በቤት ውስጥ በሚዘጋጁ መፍትሄዎች መከላከል እንደሚቻል ባለሙያዎች ይናገራሉ። እነዚህ መከላከያ መንገዶች ደግሞ የጉሮሮ መከርከርና ማቃጠልን ጨምሮ፣ የአፍንጫ መዘጋት እና መታፈን፣ ሳል፣ የፊት እና በተለይም የአፍንጫ አካባቢ መቅላት እና ህመምን መከላከል ያስችላሉ። መፍትሄ መጉመጥመጥ፦ አፍን ወደ ላይ ቀና አደርጎ ከጀርባ ወደ ኋላ ገለል በማለት ጥቂት ውሃ ወደ ጉሮሮ በማፍሰስ መጉመጥመጥ የጉሮሮ መከርከርና ማቃጠልን ለመከላከል ይረዳል።ለዚህ ደግሞ 1 የሻይ ማንኪያ ጨውን ለብ...
Read More