‹‹ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ወደ ኢትዮጵያ የመጡት ለኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትርና መንግሥት ውሸት ለማውራት ነው››
ጄኔራል ኦያይ ዴንግ አጃክ የደቡብ ሱዳን ነፃ አውጪ ግንባርን እ.ኤ.አ በ1982 ተቀላቀሉ፡፡ አገሪቱ ከዋናዋ ሱዳን ነፃ እስካወጣች ድረስ የግንባሩ ጦር ኃይል ዋና አዛዥ ነበሩ፡፡ አገሪቱ ነፃ ከወጣች በኋላ ከጦር ኃይሉ በመውጣት የተለያዩ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊነትን በመያዝ ደቡብ ሱዳንን አገልግለዋል፡፡ በተለይ ደግሞ የአገሪቱ ብሔራዊ ደኅንነት ኃላፊና የአገሪቱ ኢንቨስትመንት ሚኒስትር መሆናቸው ተጠቃሽ ነው፡፡ ጄኔራል ኦያይ በፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር በመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ተጠርጥረው ለእስር ከተዳረጉት ሚኒስትሮች መካከል አንዱ ነበሩ፡፡ አሁን ጄኔራሉ በኢጋድ የሚመራው የሰላም ሒደት ተደራዳሪ ናቸው፡፡ ወቅታዊ የደቡብ ሱዳን ጉዳዮችን አስመልክቶ የማነ ናግሽ ጄኔራሉን አነጋግሯቸዋል፡፡ሪፖርተር፡- እ.ኤ.አ. በ2013 በፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ላይ መፈንቅለ መንግሥት ለማድረግ ሞክረዋል ተብለው ተጠርጥረው ለእስር ከተዳረጉት መካከል ነዎት፡፡...
Read More