የህፃናትን የእምሮ የእድገት ደረጃ የሚያሳይ አዲስ የምርምር ውጤት ይፋ ተደረገ
የእንግሊዝ ተመራማሪዎች የህፃናት የአእምሮ የእድገት ደረጃን የሚያሳይ የመጀመሪያ የሆነውን የምርምር ውጤት ይፋ አድርገዋል፡፡ ይህ ግኝትም በመላው አለም ያሉትን ተመራማሪዎች ጤናማ የአእምሮ የእድገት ሂደትን ማወቅ ያስችላቸዋል ሲሉ ዘ ድቨሎፒንግ ሁማን ኮኔክተም የተሰኘ ፕሮጀክት ባለሙያዎች ተናገረዋል፡፡ ጥልቅ የሆነው የኤም አይ አር የምርመራ ውጤት በአእምሮ ላይ የሚከሰቱ የአዕምሮ መዛባቶችንና ኦቲዚምን ይበልጥ ማወቅ ያስችላል ብለዋል፡፡ ግኝቱ እነዚህ በአእምሮ ውስጥ የሚገኙና በቢልየኖች የሚገኙ ውስብስብ የአእምሮ ክፍሎችንም መለየት ያስችላል ተብሏል፡፡ ከ ለንደን ኪንግስ ኮሌጅ ኢምፔሪያል ኮሌጅ እና ከኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የተሰባሰቡ የጥናት ቡድኖች እንደሚሉት ይህ የምርምር ውጤት እጅግ አስቸጋሪ እና እልህ አስጨራሽ እንደነበርም ተናግረዋል፡፡ የጨቅላ ህፃናት አእምሮ በትሪሊየኖች የሚቆጠሩ ቱቦዎችና የደም ስሮች የያዙ ሲሆኑ እስከ አሁንም...
Read More