የቀሩትን የሳዑዲ የምህረት አዋጅ ትግበራ ቀናት ኢትዮጵያውያኑ እንዲጠቀሙ መንግስት ጠየቀ
የሳዑዲ አረቢያ መንግስት የመኖሪያ እና የስራ ፍቃድ የሌላቸውን የውጭ ሀገራት ዜጎች በ90 ቀናት ውስጥ እንዲወጡ ያስቀመጠው ቀነ ገደብ ቢጋመስም ወደ ሃገራቸው የሚመለሱ ዜጎች ቁጥር አሁንም አናሳ ነው። ዛሬን ጨምሮ 43 ቀናት ብቻ በቀሩት ቀነ ገደብ ተጠቅመው የሚወጡ ዜጎች ያለምንም እንግልት ወደ ሃገራቸው መመለስ የሚችሉበት እድል መመቻቸቱን ነው የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሚገልፀው። የሳዑዲ መንግስት አዋጁን ጥሰው ለሚከርሙ የውጭ ሀገራት ዜጎች ደግሞ እስራት እና ከ15 እስከ 50 ሺህ የሳዑዲ ሪያል እንደሚቀጡ ገልጿል። በሳዑዲ አረቢያ መንግስት የተሰጠው የምህረት አዋጅ እና ቀነ ገደብ ግን በዚያች ሃገር በሚገኙ እና ወደ ሃገራቸው በተመለሱ ኢትዮጵያውያን ዘንድ የተደበላለቀ ስሜትን ፈጥሯል። ከአመታት ቆይታ በኋላ በአዋጁ ምክንያት ወደ...
Read More