“ስጋት” ጠቀሜታ እንዳለው ያውቃሉ…?
የአሜሪካው የካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ያወጣው ጥናት ነገሮችን መስጋት በርካታ ጠቀሜታዎች እና በጎ ጎኖች እንዳሉት ያመለክታል። ተመራማሪዎች በጥናቱ ላይ የምንሰጋ ከሆነ የተከላካይነት እና ራስን የመጠበቅ ባህሪያችን እንዲነቃቃ ከማድረግ አንጻር ያለውን ሚና ለይተዋል። በሪቨር ሳይድ ካፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ የስነ አእምሮ ፕሮፌሰር ኬይት ስዊኒ፥ ስጋት በእኛ ላይ የሚያስከትለው መጥፎ ጎኑ እንዳለ ሆኖ መልካም ጎኖች እንዳሉት ጥናቱን በማስመልከት በሰጡት መግለጫ ላይ አስታውቀዋል። ስጋት ያለን ተነሳሽነት እንዲጨምር በማድርግ የስሜት መነቃቃትን ይፈጥራል ሲሉም ፕሮፌሰር ኬይት ተናግረዋል። ስጋት አሊያም አብዝቶ ማሰብ ከአሰቃቂ ገጠመኞች እያገገምን መሆኑን፣ ለነገሮች እቅድና ዝግጅት እደረግን መሆኑን እንዲሁም ከድብርት እያገገምን መሆኑን ሊያመላክት እንደሚችልም ጥናቱ አስቀምጧል። በጥናቱም ነገሮችን ይሰጋሉ ተብለው የተለዩ ሰዎች በስራ ቦታም ሆነ...
Read More