ለታናሿ እንዳንሰጋ
የሴቶች ጉዳይ የማይመለከተው ሰው፣ ተቋም፣ ማህበረሰብ፣ መንግስታዊም ሆነ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ወይም አገር የለም። ለዛም ነው የሴቶች ጉዳይ ቢሮዎች ማስፈለጋቸው፤ የለውጥ አስተባባሪና ቀስቃሽ እንዲሆኑ። ተመሳሳይ የሥራ ድርሻ ከተሰጣቸው መካከል ታዲያ የሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ሚኒስቴር አንዱና ዋነኛው ነው። ስለዚህ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ሥራ አፈጻጸም ላነሳ አይደለም፤ ይልቁንም ከቀናት በፊት በመሥሪያ ቤቱ የተካሄደ አንድ የጥናታዊ ጽሑፍ ጉባኤ ልነግራችሁ ነው። በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የሴቶች ጉዳይ ማካተትና ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ዳይሬክቶሬት የሚባል ክፍል አለ። ከዚህ ክፍል ተግባራት መካከል ደግሞ የውይይት መድረኮችን ማዘጋጀት አንዱ ነው። ይህንንም ተከትሎ በየሁለት ወሩ የሚካሄድ የስርዓተ ጾታ ምርምር ትምህርታዊ ጉባኤ ያዘጋጃል። ይህ ቀጥሎ ዳሰሳ ያደረግንበት መድረክ ለሰባተኛ ጊዜ የተዘጋጀ ሲሆን...
Read More