ትራምፕ ለውጭ አገራት የሚደረገው ዕርዳታ እንዲቀንስ ያቀረቡት ሀሳብ በሴናተሮች ተቃውሞ ገጥሞታል
አሜሪካ ለውጭ አገራት የምታደርገው እርዳታ በጀት እንዲቀንስ ሀሳብ ማቅረባቸው ከሴናተሮች ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡ የዴሞክራቲክ ፓርቲ አባል የሆኑት ሴናተር ክሪስቶፈር ኮንስ ይህን የተናገሩት የደቡብ ሱዳን ስደተኞችን ተዘዋውረው ከጎበኙ በሃላ እንደሆነ ተነግሯል፡፡ ከጥቂት ሳምንታት በፊት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራንፕ ሀገራቸው ለውጭ ሀገራት የምታደርገውን የእርዳታ በጀት በእጅጉ እንዲቀንስ መነሻ ሀሳብ ማቅረባቸው ጉዳዮ በሴናተሩ ትኩረት እንዲያገኝ ማድረጉን ዋሽንግተን ፖስት የዜና ምንጭ አስነብቧል፡፡ ሴናተሩ በደቡብ ሱዳን በአማፂያን ይዞታ ስር ባለችው ‹‹ጋንዮል›› በተባለች ከተማ ጉብኝት ስያደርጉ ሁሉም የመዲናይቱ ነዋሪዎች ሰብዓዊ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው በመመልከታቸው ድንጋጤ እንደፈጠረባቸው ገልፀዋል፡፡ ደቡብ ሱዳን በእርስ በርዕስ ግጭት ሳቢያ በአፍሪካ ከፍተኛ የስደተኛ ቁጥር ያላት ሀገር በመሆኗ የአገራቸው መንግስት የተለየ ትኩረት ሰጥቶ ሰብዓዊ ድጋፍ...
Read More