‹‹ሴቶች ሁልጊዜ የተሻለ ሠርተንና ልዩ ነገር ይዘን ካልወጣን በስተቀር አስቸጋሪ ነው››
ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ፣ የእናት ባንክ የቦርድ ሊቀመንበርና የሕግ ባለሙያ ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ተወልደው ያደጉት በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ ነው፡፡ የመጀመሪያና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን የተከታተሉትም በአሶሳ ከተማ ነው፡፡ ከፍተኛ ትምህርታቸውን ደግሞ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተከታትለው በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ወስደዋል፡፡ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ በኢንተርናሽናል ሪሌሽንስ አግኝተዋል፡፡ ከአሶሳ ወጥተው አዲስ አበባ ከተማን ለመጀመሪያ ጊዜ የረገጡት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሕግ ለመማር ተመድበው በመጡበት ጊዜ ነው፡፡ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ካገኙ በኋላ መጀመሪያ ወደ ሥራው ዓለም የቀላቀሉት ንግድ ሚኒስቴር ነው፡፡ ንግድ ሚኒስቴርን ከለቀቁ በኋላ በከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ሆነው ሠርተዋል፡፡ ብዙም ያልገፉበትን የዳኝነት ሥራ ለቀው በሕገ መንግሥት ኮሚሽን ውስጥ ሠርተዋል፡፡ በተለይ በሕገ መንግሥት ኮሚሽን መሥራታቸው...
Read More